ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    ቀዳሚውን የዓለም ዜና በሚከተለው የዜና መጽሔት
    -የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)የቅድመ ምርጫ ሂደቶች ላይ ጥሰቶች እንደነበሩ መግለጹ ፣በአማራ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስሞታ፣ ስለ መገናኛ ብዙኃን ምኅዳር የመንግሥት፣ የባለሙያዎች እና አጥኚዎች ዕዉነት፣
    -የነዋሪዎችን ህይወት ያቃወሰው የትራንስፖርት እጥረት በኢትዮጵያ፣
    -የሞት ፍርድን የሚጠባበቁትን ጨምሮ ሰነድ አልባዎቹ ኢትዮጵያዉያን በሳዉዲ፣
    የዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ተኩስ አቁም ወዴት ያመራ ይኾን? በተሰኙ ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ ሳምንታዊ የወጣቶች ዓለምም በሰዓቱ ይቀርባል።
    28 min
  • የሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት
    የደቡብ አፍሪቃው ዘመቻ ዱዱላ’ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን እያደነ ነው፤ የወለንጪቲ የልማት ተነሺ ገበሬዎች ካሳ አልተከፈለንም ሲሉ ማማረራቸውን፤ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮች የገበያ ተግዳሮት ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ርዳታ እንዳይቋረጥ መጠየቁ እንዲሆም ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች 10 ቢልዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዷ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    26 min
  • የሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    አሜሪካ የኤርትራን ማዕቀብ ለማንሳት ማጤኗ ለኢትዮጵያ በረከት ወይስ መዘዝ?
    ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በተለየ መንገድ የጥቃት ኢላማ መሆናቸው
    የአላማጣና አካባቢው ወጣቶች የጦርነት ሥጋትና ስደት
    የሱዳን ክስና እና የኢትዮጵያ ምላሽ
    ህወሓት ትናንት የወሰደው 'ርምጃ እና የሚኖረው ውጤት
    23 min
  • የማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    ዛሬ ታስቦ የዋለዉን 85ኛ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል መታስብያን በማስታከክ ፤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም ሲል የሚያጠይቅ ዘገባን ይዘናል። ለ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ ተግዳሮት ገጠመን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ እና የሚያሳድረዉ ጫናን የሚዳስስ ዘገቦችም በተከታታይ ይቀርባሉ። የአሜሪካዉ ትራምፕ በጀርመን ከሰፈሩ የአሜሪካን ወታደሮች መካከል ወደ 5,000 የሚሆኑትን ለማስወጣት እቅድ መያዛቸዉ እና የተሰጡ ግብረ መልሶችን የሚዳስስ ዘገባንም ይዘናል።
    19 min
  • የሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የደቡብ አፍሪቃው መጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያንን ብርቱ ስጋት ላይ ጥሏል
    አውሮፓ ሕብረት የፕሪቶሪያን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥሉ 'ርምጃዎች እንዲረግቡ ጠየቀ
    “አገልግሎታችንን ወደ አምስት ኮከብ ማሳደግ እንፈልጋለን” የኢትዮጵያ አየርመንገድ
    ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ሲታወስ
    ወደ ከተሞች የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት የቤት አቅርቦት ቀውስ ፈጥሯል-ተመድ
    24 min
  • የሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ለኦሮሚያ ክልል ዘላቂ ሰላም መፍትሄ የሚሻው የወጣቶች ምክክር ፣ በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት ያስከተለው የኑሮ ምስቅልቅል ፣ ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር የጀመረው የብትን ጭነት አገልግሎት ለኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ዕድል ፣ «በኢትዮጵያ አካታች ዕርቅ ይምጣ» የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኅበራት ጉባዔ በአሜሪካ፣ እንዲሁም አፍሪቃ ወደ ኋላ የቀረችበት የተመድ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች የትኞቹ ናቸው
    21 min
  • የሚያዝያ 20 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ።የኢትዮጵዊያን ግድያ በጆሃንስበርግ ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ምርጫ ፤ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የተረቀቀው የሳይበር ደህንነት አዋጅ ምን ይዟል? እንዲሁም የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ወቅታዊ መግለጫ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።
    21 min
  • የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በዜና መጽሔት፤ የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ መብት እንዳይገድብ መጠየቁ ፤ ምርጫ ቦርድ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚያጣራ ቡድን ማሰማራቱ፤ ከፀሐይ ኃይል የሚያመነጭ ቴክኒዎሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍሪካ የፖሊሲ አውጭዎች ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ትኩረት እንዲሰጡ የዘርፉ ባለሙያ ማሳሰባቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎች አካቷል።
    19 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…