ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በዜና መጽሔት፤ በአርሲ ዞን ሮቤ ዲዳዓ ወረዳ ንጹሐን ላይ የተፈጸመው ጥቃት፤የአፍሪካ ሃገራት በሰብዓዊ መብት ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንደማይተገብሩ ተገለፀ
    በ614 ምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንደሚያካሂድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጹ፤ ተዛብተው ተጽፈዋል የተባሉ ታሪኮች እንዲታረሙ ያሳሰበው የኦሮሞ ምርምር ማሕበር ጉባኤ ፤እንዲሁም እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት መራዘሙን የሚያስቃኙ ዘገባዎች አካቷል።
    26 min
  • የሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው እና አወዛጋቢ በሆኑት የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች የመብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ወች መግለፁን
    ኢትዮጵያ ከነዳጅ ወደ ኤለክትሪክ መኪኖች ሽግግር እያደረገች መሆኑን፤
    በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኤለክትሪክ መኪና አጠቃቀም፣ እና
    መቋጫ ባጣው የአሜሪካ እና የኢራን ውዝግብ እንዲሁም የተዘጋው ሆርሙዝ ወሽመጥ
    24 min
  • የሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ዜና መፅሄት
    የዜና መጽሔታችን በአበርገሌ ወረዳ ስለተከሰተው ግጭት፤ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሳይቀበለው መቅረቱ፤ የአውሮፓ ኮሚሽን ለአፍሪካ አገራት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት የሚውል ዕርዳታ መስጠቱ፤ እንዲሁም የአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያስተላለፉት ውሳኔና አንደምታ በተመለከተ ከብራስልሱ ወኪላችን ያደረግነው አጭር ቆይታ ይዳሰሳሉ።
    19 min
  • የሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    b,ዛሬ የዜና መጽሔታችን ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሰፊ ሥልጣን የሰጠው "የአቪዬሽን ደኅንነት" ማሻሻያ አዋጅ መፅደቅ፣ የነዳጅ እጥረት እና የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር በአሶሳ ፣’"ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እየተጣለብን ነው" ሲሉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች መግለፃቸው ፣እንዲሁም ቀነ ገደቡ እየተጠናቀቀ ያለው የተኩስ አቁም እና ተጠባቂው የኢስላማባድ ድርድር በተሰኙ ዘገባዎችን አካቷል። በቅደም ተከተል ይተነተናሉ።
    21 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዜና መጽሔት
    ህወሓት ከ2013 ዓ.ም በፊት የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወሰነ፣ ሕገወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው? ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» - አዲስ ስታንዳርድ
    16 min
  • የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    በዓለም ዜና የሚጀምረዉ የአንድ ሰዓቱ ስርጭታችን፤ በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤
    1, የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና መልስ የማግኛዉ መንገድ
    2, በአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያችን እንመለስ ጥሪ
    3, ሕገ ወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው?
    4, በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ላይ የተካሄደ ጉባኤ እንዲሁም
    5, ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊነት የሚወዳደር የጋራ ዕጩ ያላፀደቀችዉ አፍሪቃ የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።
    21 min
  • የዜና መጽሔት፤ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ሐሙስ
    በአማራ ክልል ራያ ቆቦ ወረዳ በጸበል ቦታ በደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ 8 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአደጋው ከ30 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ማኔጂንግ ኤዲተር ትላንት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከሥራ ገበታው ከተወሰደ በኋላ ዛሬም የደረሰበት አልታወቀም። ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች እና አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታጣቂዎች ተገድለዋል። በዛሬው ዜና መጽሔት ከሚቀርቡ ዘገባዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል።
    29 min
  • የሚያዝያ 7 ቀን 2018 የዜና ፅሔት
    በዜና መጽኄት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ኢሕአፓ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በሚመለከት ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ መጻፉን ገለፀ፤ ደቡብ ወሎ ዞን ፓስፖርት ለማውጣት 161 ሐሰተኛ ሰነዶች፤ የኢራኑ ጦርነት፣ ለሱዳኑ ግጭት የሚሰጠው ትኩረት እንዲቀንስ ማድረጉ ተገለፀ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የመርከቦች እገዳ በፍኖተ ሆርሙዝ ለኢራን ምን አመጣ? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ፣
    20 min
  • የሚያዚያ 6 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄት
    ዜናውን ተከትሎ በሚቀርበው የዛሬ የዜና መፅሔታችን ፤መራጮች ምን ይላሉ?፣በነጻ የንግድ ቀጠና ባለሃብቶችን ከገቢ ግብር ነጻ የሚያደርገው መመሪያ፣በአማራ ክል ተፈናቃዮች የምግብ ዕርዳታ ከተሰጠን 2 ወራት አለፉ ማለታቸውን ፣እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስሱ ጥንቅሮች አካቷል።
    ሳምንታዊዎቹ ጤና እና አካባቢ እና አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅቶችም ተካተዋል።
    23 min
  • የመጋቢት 5 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    ዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤
    የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና፤2, በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ነዋሪዎችን እየፈተነ ያለዉ የኤሌክትሪክ መቋረጥ፤ በተለያዩ የዓማር ክልል ከተሞች የንግድ ማህበረሰቡን የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ባለፈዉ ሰሞን በባሌ ሮቤ መናኸሪያ ላይ በወጣት ወንጀለኞች ተደበደቡት አባት የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።
    20 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…