ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የመጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ሀገራዊ የውይይት ኮሚሽን የትግራይ ክልልልን አጀንዳ ልየታ በአዲስ አበባ፤
    የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ እያስከተለ ያለውን ችግር
    የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ከ300 በላይ የፖሊስ መኮንኖችን ከስራ ማባረሩን እንዲሁም
    የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪቃ የባሪያ ንግድ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ መቀበላቸው የሚቃኙ አራት ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    19 min
  • የመጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    የዜና መፅሔታች በአማራ ክልል ድንገተኛ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ያደረሰው ጥፋት፤ በርዳታ አቅርቦቱ እጥረት ተፈትነናል ያሉት የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች፤ በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስላሉበት ኹኔታ ምን ይላሉ?፤ የአውሮጳ ኅብረትና የጋና የደህንነትና መከላከያ ትብብር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።
    25 min
  • የረቡዕ መጋቢት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዓለም ዜናን ተከትሎ፤
    "ከምርጭ ራሳችንን እስከማግለል ርምጃ ልንወስድ እንችላለን" ሲል የ4 ፓርቲዎች ጥንር የሆነው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ መግለፁን፤ስለምርጫው የታጣቂዎች ማስጠንቀቂያ እና የፓርቲዎች አቋም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በዛሬው ዕለት አዲስ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ልዩ መልዕክተኛ መሾሙን እንዲሁም የአሜሪካ እና የኢራን የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴን የሚቃኙ አራት ዘገባዎች ይኖሩናል።
    19 min
  • የመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    ዜና መጽሔት ጥንቅራችን አራት ዘገባዎች ይኖሩናል። እነሱም፤* በሱዳኗ ኩርሙክ የተከሰተው ግጭት የድንበር ነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ስጋት፤* የሶማሌ ክልል የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ስም በሀሰተኛ መረጃ ለማጠልሸት እየተካሄደ ነው ያለውን ድርጊት መኮነኑ፤* የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዮሐንስ ብርሃነ በአስቸኳይ እንዲፈታ ስለ መጠየቁ እና* በሰሜን ሸዋ ዞን ሰላሌ፤ በጠለፋ ምክንያት ለአስከፊ ጉዳት የተዳረገች የ7ኛ ክፍል ተማሪ ጉዳይ ናቸው።
    19 min
  • የመጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    -በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ለመሻገር ሙከራ ማድረጋቸው የተገለፀ 48 ኤርትራውያንን ማሰሩን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።
    -ጂግጂጋ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ40 በላይ ሱቆች መቃጠላቸውን የሶማሌ ክልል አስታወቀ እነዚህና
    -በዋግ ህምራ ዞን በእደ ጥበብ ባለሙያዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲሁም
    አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ አሰጣጥ ሕግ
    20 min
  • የመጋቢት 11 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዛሬው የዜና መፅሔታችን በዒድ በዓል ላይ ያተኮረ ነው። በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣በድሬዳዋ፣በሐዋሳ እና በደሴ የነበረው የበዓሉ ድባብ ያስቃኘናል።
    22 min
  • የሐሙስ መጋቢት 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት
    -በኢትዮጵያ ወቅታዊ ዲፕሎማሲ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች ፣
    -በትግራይ ክልል "አፈና እና የዘፈቀደ እሥራት" መኖሩን አንድ የሲቪክ ድርጅት መግለጹ
    አማርኛ ለምን ከአፍሪካ ህብረት የሥራ ቋንቋዎች አንዱ ሳይሆን ለምን ቀረ? -የነዳጅ ዋጋ ንረት በአሶሳ ፣ እንዲሁም የተወደደው የዒድ ገበያ በደሴ በተሰኙ ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ተካተዋል። ሳምንታዊው የባህል መድረክ በኢትዮጵያ የብርሌ ታሪክ ላይ ያተኩራል ።
    26 min
  • የመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት በአማራ ክልል የነዳጅ ዘይት እጥረት የፈጠረው የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎል፤
    ባለፉት ሰባት ዐመታት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እና ተፅዕኖው፤
    የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለዶ/ር ሲሳይ አውግቸው ተፈቅዶ የነበረውን የዋስትና መብት መሻሩ ፤ እና
    የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ቢያንስ በአንድ በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን እንቃኛን
    19 min
  • የመጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ የተፈፀሙ በደሎችና የፍትሕ ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማሕበር በካናዳ፣ እና የአፍሪቃ ሐገራት አቋም በመካከለኛዉ ምሥራቅ ጦርነት
    19 min
  • የመጋቢት 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት
    -በኢትዮጵያ የነዳጅ አጠቃቀም በቁጠባ እንዲሆን ማሳሰቢያ መሰጠቱ ፣
    - በሰሜን ወሎ ዞን ሙጃ ወረዳ በውጊያ ምክንያት መንገዶች መዘጋታቸው በነዋሪዎች ላይ ያስከተለው ማኅበራዊ ቀውስ
    - የሆርሙዝን ወሽመጥ ለማስጠበቅ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት የእርዳታ ጥሪና የአውሮጳ ኅብረት
    እንዲሁም የጀርመን የምርጫ ስርዓትና ጠቃሚ ልምዶች በተሰኙት ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    21 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…