ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የየካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው የዜና መጽሔት "በንጹሓን ላይ የሚሰነዘር" ያለው ጥቃት "እያደር ከብዷል" ሲል ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መግለጫ ማዉጣቱ፣ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና ሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ወረዳዎች፣ በተለይም በኤፍራታ ግድም እና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የተከሰተ ግጭት ፣ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    በኦሮምያ ክልል ስለመጭዉ ምርጫ ምን አስተያየት አላቸዉ ነዋሪዎችን አነጋግረናል። አሜሪካ በኢራን ላይ ልትፈጸም የምትችለው ጥቃት የምሽቱ ዜና መጽሔት የያዘዉ ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።
    26 min
  • የየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በዛሬው መጽሔታችን አምስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ብሔራዊ ምርጫ በ5 የምርጫ ክልሎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" መታዘዙ፤ ክራይሲስ ግሩፕ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ውዝግብ ያቀረበው ምክረ-ሀሳብ፤ 2025 በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ላይ "ሰፊ እሥራቶች፣ አፈናዎች እና ትንኮሳዎች የተጋረጡበት" ነበር መባሉl ፤ «የምግብ ድጋፍ ተነፈግን» ያሉ ተፈናቃዮች ለከፋ ስቃይ ተዳርገናል ማለታቸው ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።
    25 min
  • የየካቲት 18 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    -የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንት ፍቃዱን የሰረዘበት አዲስ ስታንዳርድ ሥራዉን አለማቋረጡን አስታወቀ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ትናንት ባሰራጨዉ ደብዳቤ የአዲስ ስታንዳርድ የምሥክር ወረቀት መሰረዙን አሰታዉቆ ነበር።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ያደረጉት ዓመታዊ የመርሕ ንግግር በአብዛኛዉ ሐሰትን ከዕዉነት የቀየጠ መሆኑን አጥኚዎችና ተንታኞች አስታወቁ።ትራምፕ በኢራን ላይ የሰነዘሩት ዛቻም ከቴሕራን ጠንካራ አፀፋ ገጥሞታል። --በግሪጎሪያኑ አምና 2025፣ 129 ጋዜጠኞች መገደላቸዉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ CPJ አስታወቁ።አብዛኞቹን ጋዜጠኞች የገደለችዉ እስራኤል ናት።
    23 min
  • የየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    ዜና መጽሔት የአፍሪካ ቀንድ ለውጭ ኃይላት ፍላጎት ማስፈፀሚያነት ያለው ተጋላጭነት ፤
    ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት በኢትዮጵያ ሠፋ ወይስ ጠበበ ?፤
    ለተሻለ ሁኔታ ወደ አረብ ሃገር የሚሰደዱ የኢትዮጵያ ወጣቶች፤
    እንዲሁም በአዉሮጳ አባል ሃገራት ተቃዉሞ የታገደዉ ለዩክሬይን ይሰጣል የተባለዉ ብድር
    ፤የተሰኙ ዘገባዎችን ያስተነትናል።
    20 min
  • ነዋሪዎችን ያሰጋው በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ዳመና
    በትግራይ ክልል ሌላ ዙር ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋት ላይ መውደቃቸውን እየገለጹ ነው፡፡አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ጦርነት ይከሰታል በሚል ስጋት ወደ አገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች እየወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
    4 min
  • በትግራይ አንዣበበ ያለውን የጦርነት ድባብ በሰላም እንዲፈታ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ጠየቀ
    ትግራይ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ያንዣበበ" ያለው "አስፈሪ" የጦርነት ድባብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲገታ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተቋማት መሪዎች ግልጽ ደብድቤ ጽፏል።
    4 min
  • በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ እገታ፣ ግድያና ዝርፊያ እያደረሱ ነው ተባለ
    በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ እገታ፣ ግድያና ዝርፊያ እያደረሱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ በተለይም በሞቱማ፣ ጀልደይቲ፣ ጉሬ እና መልካሉጎ ቀበሌዎች ታጣቂዎቹ እንደሚገድሉና እያገቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል።
    4 min
  • የዐርብ የካቲት 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና መጽሔት
    የምሽቱ ስርጭታችን በዜና መጽሔት ጥንቅሩ
    --ከጦርነት ሥጋት ያልተላቀቀው ኢትዮጵያን፣ ሱዳንን እና ኤርትራን የሚያዋስነው አካባቢ
    --እየሰፋ የመጣው የምንዛሪ ቢሮዎች እና የባንኮች ልዩነት
    -- እናት ፓርቲ "ለኢትዮጵያ" ወደተባለው የፓርቲዎች ቅንጅት መመለሱ ተገለጠ
    -- የተማሪዎች ምገባ በአማራ ክልል-- እንዲሁም
    --ነዳጅን ከመደበኛ ዋጋ የመሸጥ ፈተና -- ፤የተሰኙ ዘገባዎችን በስፋት ያስተነትናል።
    26 min
  • የዜና መጽሔት፤ የካቲት 12 ቀን 2026
    ዜና መጽሔት ፤ -የየካቲት 12 ሰማዕታት ፍትሕ እንዲያገኙ የሚጠይቀው ዓለም አቀፍ ዘመቻ -የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የምዕራብ ኦሮሚያ ጉብኝት -የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል አጀንዳዎችን አዲስ አበባ ላይ ለማሰባሰብ መወሰኑን ማስታወቁ -“የጦርነት ድባብ” እና የኦነግ ማሳሰቢያ- በአማራ ክልል ያለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት -
    ከሶማሊያ እና ሳውዲ አረቢያ ወታደራዊ ስምምነት ጀርባ ያለው ምንድን ነው በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ቀርበዋል።
    29 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…