ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የዜና መጽሔት፤ የካቲት 12 ቀን 2026
    ዜና መጽሔት ፤ -የየካቲት 12 ሰማዕታት ፍትሕ እንዲያገኙ የሚጠይቀው ዓለም አቀፍ ዘመቻ -የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የምዕራብ ኦሮሚያ ጉብኝት -የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል አጀንዳዎችን አዲስ አበባ ላይ ለማሰባሰብ መወሰኑን ማስታወቁ -“የጦርነት ድባብ” እና የኦነግ ማሳሰቢያ- በአማራ ክልል ያለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት -
    ከሶማሊያ እና ሳውዲ አረቢያ ወታደራዊ ስምምነት ጀርባ ያለው ምንድን ነው በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ቀርበዋል።
    29 min
  • የየካቲት 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። የቱርክዬ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት፤ በሕወኃትና በፊደራል መንግስት ዳግም ግጭት እንዳይቀሰቀስ የነዋሪዎች ሥጋት፤ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ወጪ የድሬደዋ የፍሳሽ ማስወገጃ እና ማጣርያ ፕሮጀክት፤ ደቡብ ወሎ ዞን ከ276 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት አልተመለሱም፤ እንዲሁም ቱሪዝም እያበበ ነው የተባለለት አዲሱ የጎርጎሳውያን ዓመትና የኢትዮጵያ ድርሻ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። ሳምንታዊዎቹ ከኤኮኖሚው ዓለም እንዲሁም ሣይንስና ቴክኖሎጂም ተዘጋጅተዋል ።
    21 min
  • የየካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣ ወታደራዊ ንቅናቄ በሰሜን ኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአቪሽን ፀጥታ ላይ ያደረገዉን ዉይይት። የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 6 ወራት ከ41 ኩንታል በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱን አስታዉቋል።አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ 15 ሰዎች መገደላቸዉ ተዘግቧል።የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) በክክሉ ፀጥታና የኑሮ ዉድነት ላይ ያደረገዉ ዉይይት ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ። ዜና መፅሔቱ ደቡብ ወሎ ዞን 276 ሺሕ ተማሪዎች ትምሕርት ማቋረጣቸዉን ይቃኛል። ሳምንታዊ ጤናና አካባቢ ምዕራብ ሸዋ ዉስጥ ምንነቱ በዉል ያልታወቀ አዉሬ ያደረሰዉን ጥቃት ይዳስሳል።
    24 min
  • የየካቲት 9 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    -ባለ ጉዳይ የበዛበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና፤
    --በአፍሪቃ በቀጠሉ የፀጥታ ችግሮችና በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎች በማሳለፍ የተጠናቀቀዉ 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ፤
    --የምርጫ ዝግጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
    --በደቡብ ኢትዮጵየ ክልል በየዞኖቹ የተዘረጉ ህገ ወጥ ኬላዎች እና ተግዳሮቶቻቸዉ
    20 min
  • የየካቲት 6 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎች በትንታኔ ይቀርባሉ ። ለጸጥታ ቅድሚያ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ፤ ሕዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ ለአፍሪቃ ህብረት የላከው ደብዳቤ እና አንድምታው ፤ በደብረታቦር ከተማ የተከሰተው የጸጥታ አለመረጋጋት እና የነዋሪው አስተያየት ፤ የኢትዮጵያውያን ሕብረትና የሽግግር ቅድመ ሁኔታ ላይ የተደረገ ምክክር እና አንድምታው፤ የአውሮጳ መሪዎች ከኤኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ የያዙት መንገድ የተመለከቱ ዘገባዎች ይደመጣሉ ።
    24 min
  • የየካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዙ 19 ማሻሻያዎች አድርጓል።
    የሳዑዲ ማረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የኢትዮፕያ ጉብኝት እና አንድምታው
    ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ተፈናቅለው ለሁለት ዓመታት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ተጠልለው ከቆዩ ተፈናቃዮች መካከል ከ1,200 በላይ የሚሆኑት ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ገልጸዋል።
    19 min
  • የየካቲት 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዕለቱ መጽሔታችን ሶስት ርዕሰ ጉዳዮችን በቅደም ተከተል ያስደምጣል። የሱዳን የርስ በርስ ግጭት፤ አፍጦ የመጣው ጣልቃ ገብነት እና ጂኦፖለቲካው፤ ቆቦ ዙሪያ የሰፈሩ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ ሳያገኙ ሁለት ሳምንት እንዳለፋቸው መናገራቸው፤ የአብን የፖርላማ ተመራጮች ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ የወሰዱት አቋም በሚሉ ርዕሶች የተሰናዱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው
    15 min
  • የየካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ክስ ዛሬ ሰኞ “ሐሰት” በማለት አጣጥሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ የድንበር አካባቢ ከዚህ ቀደም ከተቆጣጠሩት “የበለጠ ዘልቀው” እንደገቡ ገልጸው ነበር። በጉዳዩ ላይ የተንታኞች እና የፓለቲከኞች አስተያየቶች የተካተቱባቸው ዘገባዎች ለዛሬ ተዘጋጅተዋል። የአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 625,000 የሥራ ዕድሎች በክልሉ እንደተፈጠሩ አስታውቋል። ይህን የተመለከተው ዘገባ በዜና መጽሔት ከሚቀርቡት መካከል ነው።
    17 min
  • DW Amharic የጥር 29 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች የመከላከያ ዝርዝር እንዲያቀርቡ መታዘዙን፤ ከ16 ሺህ በላይ ህገወጥ ስደተኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን የአፋር ክልል ፖሊስ ገለጸ፤ በትግራይ የነዳጅ ዋጋ በእጥፍ ስለመጨመሩ፤ የአሜሪካና የኢራን ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት፤ የመንግሥታት አስተያየት ያልተለየው የሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይ
    30 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…