Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
January 29የጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበዜና መጽሔት ዳግም እየተስተዋለ የመጣው የሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ሥጋት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ የነበረውን በረራ ማቋረጡ እና የተፈጠረው ውጥረት፣ ኢትዮጵያ የጠየቀችው የዓለም ባንክ ድጋፍ አንድምታ፣ ቅንጅት የመሰረቱ ፓርቲዎች ከአሜሪካ ኤምባሲ መሪዎች ጋር ተወያዩ፤ እንዲሁም “ሰላሌን በጅምላው ተሳድበዋል” የተባሉ ፓስተር በቁጥጥር ስር ዋሉ በሚል ርዕስ የተቀናበሩት ዘገባዎች ይቀርባሉ።28 minPlay
January 28የጥር 20 ቀን 2018 የዜና መፅሔትበዜና መጽሔት የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ ከ80 በላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሚሊሽያዎች እጅቸውን ሰጥተዋል ሲል የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ማስታወቁ፤ በአማራ ክልል ጦርነት የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል መባሉ እንዲሁም ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ በማሻገር እና ማሰቃየት ከቤተሰቦቻቸውም ገንዘብ በመቀበል ወንጀል የተከሰሰው ኤርትራዊ ላይ የኔዘርላንድ ፍርድ ቤት የ20 ዓመት እስር መበየኑን ያስቃኘናል19 minPlay
January 27የጥር 19 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔትብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ በንግድ ሥርዓት ማሻሻያ እና በዋጋ ንረት ስጋት መካከል፤ ናዚ የፈፀመው የሆሎኮስት እልቂት መታሰቢያ በአዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አቅርቦት እና የሚነሱበት ጥያቄዎች ብርቱ የበረዶ ወጀብ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረሰው የሕይወትና ንብረት ጥፋት19 minPlay
January 26የጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መፅሔታችንምርጫ እና የመገናኛ ብዙኃን ያሉበት ወቅታዊ ኹኔታየጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያና የባለሙያ አስተያየት8 ፓርቲዎች የፖለቲካ ምኅዳር እያጨለሙ ያሉ ችግሮች ገጥመውናል ማለታቸው፣ እንዲሁምከሰሜን ምሥራቅ ኬኒያ ማንዴራ ከ9 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ግዛቲቱን ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ያስቃኘናል18 minPlay
January 23የዐርብ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር ታጠናክራለች ተባለ፤ አዲሱ የአማራ ክልል የተቋማት አደረጃጀት የሠራተኞች ቁጥር መቀነስ ትኩረቱ አለመሆኑ ተነገረ፤ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት "የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ" ሥራዎችን በበላይነት እንዲያስፈጽም ሥልጣን ሊሰጠው ነው፤ ግሪንላንድ በዳቮሱ ጉባኤ፣ ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ፍጥጫ23 minPlay
January 23የጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር ታጠናክራለች ተባለ፤ አዲሱ የአማራ ክልል የተቋማት አደረጃጀት የሠራተኞች ቁጥር መቀነስ ትኩረቱ አለመሆኑ ተነገረ፤ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት "የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ" ሥራዎችን በበላይነት እንዲያስፈጽም ሥልጣን ሊሰጠው ነው፤ ግሪንላንድ በዳቮሱ ጉባኤ፣ ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ፍጥጫ23 minPlay
January 21የጥር 13 ቀን 2018 የዜና መጽሔትበዜና መጽሔት፤ ከወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ተፈናቅለው ላለፉት ስድስት ዓመታት በአማራ ክልል በመጠለያ የሚገኙ ወገኖች ወደኖሩበት ቀዬ እንዲመለሱ መጠየቃቸው፤ በጉጂ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉ፤ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ጉብኝት ፤ በትራምፕ የግሪንላንድ እቅድ ምክንያት በምዕራባውያን ሃገራት መካከል የቀጠለው ውዝግብ፤ እንዲሁም ዳቮስ ስዊዘርላንድ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ጉዳዮች ጉባኤን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።22 minPlay
January 20የዜና መጽሔት፤ ጥር 12 ቀን 2018 ማክሰኞየዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያ የመገበ,ያያ ገንዘቧን ሐገር ዉስጥ ለማተም ማቀዷ የሚኖረዉን ፋይዳና ሥጋት የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ በደቡብ ኢትዮጵያ አለቅጥ የናረዉ የመጓጓዣ ዋጋ የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ማወኩን፣ አማራ ክልል አበርገሌ ወረዳ የመድፍ ጥይት ሲቀጠቅጡ 6 ሰዎች መሞታቸዉን የሚተነትኑ ዘገቦችም አሉት።ሳምንታዊዉ ጤናና አካባቢ የደን መራቆትን ለመከላከል የማሕበረ-ሰብ መሪዎች የሚያደርጉትን ጥረት ይዳስሳል።15 minPlay
January 19የጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየጥምቀት በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ፤ በሃዋሳ እና በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ላይ የተካሄደዉን አከባበር እንዴት እንደነበር እንቃኛለን። በኮየፈጬ ሸገር ከተማ ትናንት የከተራ በዓልን በማክበር ላይ ሳሉ የኤልትሪክ አደጋ ስለደረሰባቸዉ አራት ወጣቶች ጉዳይም የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሌላዉ የሚዳስሰዉ ጉዳይ ነዉ።17 minPlay