ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • በምርጫ ቦርድ እውቅናው የተሰረዘው ሕወሓት፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ያወጡትን መግለጫ ነቀፈ
    በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ሑመራ ከተማን ከጎበኙ በኋላ ያወጡት መግለጫ፤ በፕሪቶሪያ ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ፈራሚዎች መካከል አለ ያለውን "ሰፊ ​​ክፍተት ከማጥበብ ይልቅ የሚጎዳ ሂደትን የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል" ሕወሓት ባወጣው መግለጫ ገለልጿል።
    4 min
  • “ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከቀዳሚ አጀንዳዎቼ አንዱ ነው” ዶናልድ ትራምፕ
    የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤ ግብጸጽ እና ኢትዮጵያን ዳግም ወደ ድርድር ለስገባት አገራቸው አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ፡፡ትራምፕ ይህንን ያሉት ለግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱፈታ አልሲሲ ብለው ትሩዝ ሶሻል በሚባለው የማህበራዊ መገናኛ ዘዲያቸው ላይ ባጋሩት ደብዳቤ ነው።
    5 min
  • የጥር 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሑመራ ጉብኝት፤
    በሲዳማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ ሁለት ጥንዶችን ጨምሮ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፤
    በኢትዮጵያ የተከሰተው ቀዝቃዛ የአየር ጸባይና ጉንፋን ፤
    የአሜሪካ የስደተኝነት ቪዛ እገዳና
    የዝነኛው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ህልፈት
    28 min
  • በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የትናንቱ መግለጫ ምን ያመለክታል?
    በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ "በሑመራ ደማቅ አቀባበል" እንደተደረገላቸው የሚገልጽ ነው። አምባሳደሩ በስፍራው ያሉ ሰዎች "የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በዐይኔ ተመልክቻለሁ" ብለዋል።
    5 min
  • የጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ስምንት ፓርቲዎች ሀገራዊ ምክክር በክልሉ እንዲካሄድ ለማገዝ ተስማምተዋል። በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት የአድማ ብተና እና የመደበኛ ፖሊስ አባላት የታጠቁትን የጦር መሣሪያ እንዲያስረክቡ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ዛሬ ያበቃል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከዛሬ 11 ሰዓት በኋላ “የጦር መሣሪያ በእጁ የተገኘ እንደ ፀረ-ሠላም ተቆጥሮ” እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር። በዛሬው ዜና መጽሔት ከሚቀርቡ ዘገባዎች መካከል ሁለቱ ይገኙበታል።
    20 min
  • የረቡዕ ጥር 6 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዓለም ዜናን ተከትሎ፤ በሚቀርበው የዜና መጽሔት ጥንቅር
    በኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰሞኑ ቃለምልልስ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች
    ያወዛገበው የአባገዳዎች ሽምግልና ሂደት
    የሶማሊያ ካቢኔ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን እና ትብብርን በሙሉ ማገዱን፣
    የአውሮፓ ህብረትም እና አሜሪካ ለኢራን ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን፤ የሚያስቃኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።
    20 min
  • የጥር 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    ፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥርና ሀገር የሚገባው የፖለቲካ ምኅዳር፤ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ንግግር፤
    የመንግስት ገቢ መጨመር እና የታክስ ከፋዩ እሮሮ፤
    ሁለት የቱርኪዬ ዜጎች እና አንድ ኢትዮጵያዊ በታጣቂዎች መገደላቸው
    በኖሌ ካባ ወረዳ በግዲያና ዝርፍያ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው
    28 min
  • የጥር 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    መጽሄተ ዜናችን አራት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ ያስደምጣል። የጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ወደ ጂቢቲ ጉዞ እና ወቅታዊ ሁኔታ ፣ በአዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃዉሞ እና የመንግስት ምላሽ ፤ በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን የምግብ እጥረት የፈጠረው መፈናቀል ፤ እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልሎች አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች መወለዳቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች ይደመጣሉ።
    19 min
  • የታኅሣሥ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ዝቅተኛ የወለድ ተመን በገበያ እንዲመራ መወሰኑ እና አንደምታዉ
    የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅቶች ስምምነት
    ታጣቂዎች በመስቃን እና ማረቆ የፈጠሩት ሥጋት
    ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ፖሊስ የፈፀመዉ ግድያ ከፍተኛ ቁጣና ተቃዉሞ ማስነሳቱ
    ከምሁራን የሚጠበቀው አገራዊ ግዴታና ገቢራዊነቱ?
    23 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…