ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የታኅሣሥ 28 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዓለም ዜናን በሚከተለው በዜና መጽሔት፤ የበዓል ዋዜማ እንደመሆኑ የበዓል ገበያና ዝግጅቶችን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ከላሊበላ፤ ከአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ደርሰውናል፤ እንዲሁም ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አዲስ ዋና ዳይሬክተር መሾሙን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    20 min
  • የታኅሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤በኢትዮጵያ እየጠነከረ የመጣው የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ፤በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የሚገኙ ከ12 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እያሰሙ ያሉት ሮሮ
    እንዲሁም ከምሁራን የሚጠበቀው አገራዊ ግዴታና ገቢራዊነቱ? የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት ያስተነትናል።
    15 min
  • የታኅሣሥ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣
    በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ለምን አቃተ?
    የናፍጣ አጥረት በደቡባዊ ኢትዮጵያ ከተሞች ፣
    "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅ ማግኘቱ ፣
    ላሊበላን የሚጎበኙ የውጭ ጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ ነው መባሉ
    24 min
  • የታኅሳስ 23 ቀን 2008 ዓም የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ፤ የቀድሞው የሰላም ሚኒስቱር ሚኒስትር ዴኤታ ታዩ ደንደአ የፍርድ ቤት ውሎ፤ የተከሳሾች የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት ጉዳይ፤ የሰላም ጉባኤ በጋምቤላ፤ በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ የተያዙ በርካታ ወጣቶች ወደ የቤተሰቦቻቸው መመለሳቸው እንዲሁም የቻይና ወታደራዊ ልምምድና የታይዋን ዛቻን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    24 min
  • የታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    -ኢትዮጵያውያን እና ያላባራው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ፣
    -የሰነድ አልባ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እሥር በኬኒያ፣
    ብሪታንያንና ካናዳን ጨምሮ ዐሥር አገራት«አደገኛ» ስላሉት የጋዛ ሰብአዊ ሁኔታ ያወጡት ማስጠንቀቂያ፣
    የቀነኒ አዱኛ ቤተሰብን ከአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጋር ለማሸማገል የተደረገው ባህላዊ የእርቅ ጥረት የተደናቀፈበት ምክንያት
    22 min
  • የታኅሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዛሬው የዜና መጽሔት፤ ቀዳሚው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በወቅታዊ አካባቢያዊ እና ዲፖሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን ማብራሪያን የሚቃኘው ዘገባ ነው፤ በአማራ ክልል የዘንድሮ የትምህርት ዘመን እስካሁን ለመማር የተመዘገቡት ተማሪዎች በክልሉ ካሉት 36 በመቶው ብቻ ናቸው መባሉ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ በሚያዋስናት የድንበር አካባቢ ከሚገኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ታጣቂዎች የጥቃት ስጋት አለብኝ ስትል መክሰሷ እንዲሁም የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ያለመው የትራምፕ ፑቲን የስልክ ውይይትና የዘለንስኪን ጥርጣሬ የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል።
    22 min
  • የታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓም የዜና መጽሔት
    በደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳት፤
    አዲሱ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የጤና ስትራቴጂና አንደምታው፤
    የቀይባሕር ዓፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የቀይባሕር ብሔራዊ ኮንግረንስ የጋራ ስብሰባ በአዲስ አበባ፤
    እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅናና የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ምላሽ
    17 min
  • የታኅሣሥ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ "የፖለቲካ ፍላጎት" ማራመጃ እየሆነ ነው መባሉ ፤
    የኢትዮጵያ ብር በዓለማቀፍ ደረጃ በመግዛት አቅሙ እጅግ ደካማ ከተባሉ የመገበያያ ገንዘቦች ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፉ ፣
    በሰሜንና ደቡብ ወሎ በካምፕ ዉስጥ የሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ የመንግስት ድጋፍ መጠየቃቸው፣
    የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያው ርዕሰመስተዳድር አቶ ሀሰን አሊ ከ27 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገር ቤት ስለመመለሳቸው ፣
    ከትግራይ ክልል ደንጎላት እና አማራ ክልል ከዋግ ህምራ ብሄረሰብ ዞን ፃግብጂ ወረዳ የመጡ ህፃናት ለልመና እድሜያቸዉን ለማይመጥን ስራ መዳረጋቸው
    24 min
  • የታኅሳስ 16 ቀን 2018 ዓ/ም ዜና መጽሔት
    የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን ትግራይ ክልል ውስጥ ተፈናቃዮች ለረሀብ ተጋልጠዋል መባሉን ትክክል አይደለም ብሏል
    ከትናንት ምሽት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለባት ጋምቤላ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ
    ምርጫ ቦርድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዜጎችን የመደራጀትና የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረት ዴሞክራሲያዊ መብት እያስተጓጎለ ነው ማለቱ
    እንዲሁም የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት የኤርትራ መንግሥት የሰብአዊ መብቶችን ጥሷል ሲል በ120 ገጽ የተሰነደ አቤቱታ ለአፍሪቃ ሕብረት ማቅረቡ
    20 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…