ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሐሙስ ጥር 28 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሄት
    የዓለም ዜናን ተከትሎ፤በሚቀርበው የዜና መፅሄት ጥንቅራችን ፤
    ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ እና የፀጥታ ተግዳሮት፤
    ብሔራዊ ቋንቋና ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራን ጨምሮ 17 አጀንዳዎች ለምክክር ኮሚሽን ቀረበ መባሉን፤
    ለጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ኹኔታን በሚመለከት የተደረገ ውይይትን፤
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ምዕራፎች ለተማሪዎች እንዳይሰጡ ማገዱን፤
    በዚህ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ዕውቁ ኤርትራዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አስምሮምን የሚዘክር ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።
    26 min
  • የመጭውን ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ኹኔታ የተመለከው ውይይት
    ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎችን "የፀጥታ ኹኔታ" በተመለከተ "ከባለድርሻ አካላት ጋር" ሰሞኑን ውይይት አድርጓል።ውስን የመገናኛ ብዙኃን ለመክፈቻው ብቻ ተጠርተው ውይይቱ ላይ ባልተጋበዙበት በዚህ ውይይት ላይ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ?
    5 min
  • ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ እና የፀጥታው ተግዳሮት
    ኢትዮጵያ በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት መሆኗን በምርጫ አስፈጻሚው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አሳውቃ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ በዚህ ላይ አስተያየታቸውን የሚሰጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን ለማድረግ አስቻይ የፀጥታ ሁኔታ የለም በማለት ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡
    5 min
  • ብሔራዊ ቋንቋና ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራን ጨምሮ 17 አጀንዳዎች ለምክክር ኮሚሽን ቀረቡ
    በቅርቡ ከመንግሥት ጋር "የሰላም ስምምነት" መፈረሙን የገለፀው "የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት" የተባለዉ ታጣቂ ኃይል አካል የሆነ ቡድን "አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን፣ ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራ እንዲከናወን የሚሉትን ጨምሮ 17 አጀንዳዎችን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን ገለፀ።
    5 min
  • የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የተወሰኑ ምዕራፎችን አገደ
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ምዕራፎች ለተማሪዎች እንዳይሰጡ አገደ ፡፡ መምሪያው እገዳውን የጣለው በመማሪያ መጽሀፍት ውስጥ “ የውሸት ታሪኮች” ተጽፈዋል በሚል ነው ፡፡
    4 min
  • በገዳ ስርዓት ላይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ሲታወሱ
    የኦሮሞ የገዳ ስርዓትን ለግማሽ ምዕተ-ዓመት በማጥናት ለዓለም ያስተዋወቁት ትውልደ ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ህልፈተ ህይወታቸው መሰማቱ በበርካቶች ዘንድ ሀዘን ፈጥሯል፡፡
    ተመራማሪው የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ አይነተኛ ሚና መጫወታቸውም ይነገራል።
    5 min
  • የጥር 27 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ ፈጽሟል ስለተባለው ውድመት የተሰጡ አስተያየቶች፤ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ይዞታ እና የአገራት ፍላጎት፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ጉባዔ በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ መከረ? እንዲሁም አማራ ክልል በጦርነት ትምህርት ቤት መዘጋትና በሴቶች ላይ ያለ እድሜ የግዳጅ ጋብቻ
    20 min
  • የጥር 26 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    የኢትዮጵያና ኤርትራ ፀብ የተፋፋመው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈረም ነው ፤ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ መልሶ በረራ መጀመር እና የፈጠረው መረጋጋት፤ ግጭት ሸሽተው በቆቦ የሰፈሩ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፤ በኦሮሚያው ግጭት ለደረሰው ሰብአዊ ጉዳት እና የኦነሰ አዛዥ ምልከታ እና አንድምታው
    21 min
  • የጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስለ ሰሞኑ ኹኔታ መግለጹ፣ በቆቦ ከተማ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር እና የሰብአዊ ድጋፍ መዘግየት፣ ኢዜማ በአባላቱ ላይ “ሕገ-ወጥ እስር እና እንግልት” በአስቸኳይ እንዲቆም መጠየቁ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ስለሙስና ያስተላለፉት መልእክት አንድምታ
    19 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…