ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የመጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽኄት የ«ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ፡ በቴክኖሎጂ እድገት እና በዜጎች መብት መካከል ያለው ሚዛን፤ የጦርነት ስጋት ያዣበበባት ትግራይ ክልል እና የህወሓት አስገዳጅ የገንዘብ ማሰባሰብያ ፤ በአዲስ አበባ እና ደሴ መንገድ የአሽከርካሪዎችና ተጓዦች የደኅንነት ሥጋት ማየሉ፤ ነጻ ሚዲያ የሚኖረው ሚና ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቁ፤ እንዲሁም የጀርመን የፌዴራሊዝም ሥርዓት አተገባበር እና ልዩ መገለጫው ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።
    27 min
  • የመጋቢት 2 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዓለም ዜናን በሚከተለው የዜና መጽሔት በኢትዮጵያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን አሰመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በጋሞ ዞን በናዳና ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 64 መድረሱ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው እና የኑሮው ጫና እንዲሁም በፖላንዱ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፕዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቶች ቡድን ያጋጠመው የቪዛ ችግርን ይዳስሳል።
    20 min
  • የየካቲት 30 ቀን 2018 ዓም የዜና መጽሔት
    --በጦርነት ግጭት ዉስጥ የሴቶች ከፍተኛ ተጋላጭነት እልባት ያሻዋል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ)መግለጫ ማዉጣቱ
    --የአፍሪካ ሕብረት የሴቶችን ውክልና የበለጠ እንዲያሳድግ መጠየቁ
    --የሲቪል ነዋሪዎች ደህንነት እንዲጠበቅ የጠየቀዉ ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ
    --በደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን አምራቾች በሰላም እጦት ምክንያት ስጋት ውስጥ ነን ማለታቸዉ እንዲሁም
    -መዲና በርሊን የሚገኘዉ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ እና የጀርመንን ግንኙነት የተመለከተዉ ስብሰባ
    23 min
  • የየካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ -ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ፣ሴቶችን በጅምላ የመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መክሰሱ ፣
    -ነገ ስለሚጀመረው የመራጮች ምዝገባ የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች፣
    -በኢትዮጵያ በኬንያና በሶማሊያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለድርቅ መጋለጣቸው
    -ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የ"አንድ ቀን ውድድር" እንደምታዘጋጅ መገለጹ
    20 min
  • የየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን
    41 ሐገሮች በኢትዮጵያ ያለውን የመናገር ነጻነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን፤
    የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሞሽን በአርሲ ስለተገደሉ ዜጎች ያወጣውን መግለጫ፤
    ከራያ አላማጣ፣ ኮረምና ኦፍላ ዛታ የተፈናቀሉ ወገኖች የዕርዳታ ጥሪ፤
    በምዕራባዊ የሐገሪቱ ክፍል ከመደበኛ በላይ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን፣
    በኢትዮጵያ የተከሰተው የነዳጅ ዕጥረት እንዲሁም የድሬደዋ ስታድየም - የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ጋር የሚያደርገውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንዲያስተናግድ መወሰኑ" የተሰኙትን ጉዳዮች ያስቃኘናል
    28 min
  • የየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ያገረሸው ጸጥታ ችግር፤ በአማራ ክልል የሚካሄደው ውጊያ ወጣቶች ላይ ያስከተለው ተጽዕኖ፤ ምርጫ ቦርድ በ5 የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ለቀረበበት ክስ ለፍርድ ቤት ምላሽ ማቅረቡ፤ የሱዳን መከላከያ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ክስ አንድምታ
    31 min
  • የማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    በዛሬው የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ ለታቀደዉ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማሕበራት ድርጅቶችን ዝግጅቶች የሚቃኙ ሁለት ዘገባዎችን ፣ የአድዋ ድል 130ኛ ዓመት ዝክር በፓሪስ የሚመለከት ዘገባ የእስራኤልና የአሜሪካ ድብደባና የኢራን አፀፋን የሚመለከት አጭር ቃለ መጠይቅም ተካቷል።
    14 min
  • የየካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    130ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ በድሉ መታሰቢያ ማዕከል ተከብሯል፤
    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ጃዊ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን የጅምላ እልቂት አውግዛለች፣
     አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራንን አጸፋንና አውሮጳን እንዲሁም ጦርነቱ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በቀጥታ ሊጎዳ ይችላሉ መባሉ
    21 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…