ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • DW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 ዜና መጽሔት
    የነዳጅ እጥረት፣ የመጓጓዣ ዋጋ እና የጤፍ አቅርቦት፤ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመር፤ ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ሕብረት የሠላምና ፀጥታ ምክር ቤት የአንድ ወር ሊቀመንበር ሆነች፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ተኩስ አቁም ያሳደረዉ ተስፋ በኢትዮጵያ፤ የአሜሪካና ኢራን ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት
    24 min
  • የመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ ም ዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣የትግራይ ክልል ጊዚያዊ ፕሬዝደንት የጄኔራል ታደሰ ወረደ ዘመነ-ሥልጣን ለተጨማሪ አንድ ዓመት መራዘሙንና ያስከተለዉን ቅሬታ የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞንን የመታዉ ድርቅ ከሁለት ወረዳ ብቻ ከ4000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተሰምቷል።የአፍሪቃ ሕብረትና የኢትዮጵያ መሪዎች በአንጋፋዋ ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ሞት የተሰማቸዉን ሐዘን እየገለፁ ነዉ። ዜና መፅሔቱ ዩናይትድ ስቴትስ፣ እስራኤልና ኢራን ለሁለት ሳምንት ተኩስ ማቆማቸዉን፣ ምክንያቱንና የወደፊቱን ሁኔታ በተመለከተ ከባልደረቦቻችን ጋር የቀጥታ ዉይይት ይሰማበታልም።
    33 min
  • የመጋቢት 29 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    በዜና መጽኄት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ዘገባዎቹ፦ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል?፤ በነዳጅ እጥረቱ የተስተጓጎለው ትራንስፖርትና መጪው የበዓል ሸመታ፤ የነዳጅ እጥረት በአማራ ክልል የፍትህ ስርዓት ላይ እንቅፋት እየሆነ ነው መባሉ ይሰኛሉ ። እንዲሁም የዪናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን የሰጡት ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ጫፍ መድረሱ እና ያጠላው ሥጋት የሚዳስስ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል
    18 min
  • የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ማራዘሙ
    በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ የፈጥረው ተፅዕኖ የለም መባሉ
    በአረብ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እሳት እየለበለባቸው የሚያገኙትን ገንዘብ እንዲያጠራቅሙላቸው ወደ አገር ቤት ሲልኩ መከዳታቸው
    የአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር በር ለመክፈት ስምምነት ላይ እንድትደርስ የሰጡት ቀነ ገደብ ነገ ያልቃል በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን አጭር ቆይታ ይኖረናል።
    18 min
  • የመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዜና መፅሄት
    በዛሬው የዜና መፅሔታችን በጅቡቲ መኪኖቻቸው ያለስራ የቆሙባቸው የነዳጅ ጫኝ ቦቴ አሽከርካሪዎች ምሬት፤የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ፤ኢትዮጵያ አሳካሁ ያለችው የ13 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት አንድምታ፤እንዲሁም አዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።
    23 min
  • የመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የስደተኞች ሰቆቃ በየመን እና በሳውዲ አረቢያ ድንበር ላይ
    በትግራይ ክልል እና ውዝግብ ባለባቸው ቦታዎች የመራጮች ምዝገባ ምን ይመስላል?
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን መምራት የጀመሩበት ስምንተኛ ዓመት
    የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ ማዳከም ጀምሯል
    ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኢራን ጦርነት ለህዝባቸው ያስተላለፉት መልዕክት
    26 min
  • የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ዝግጅታችን አዲስ አበባ ውስጥ የተሰየመው የትግራይ ምክክር እና አንድምታው፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዲሱ “የህገወጥ ቤቶች ግንባታ” ደንብ እና ያስተናገደው አስተያየት ፤ገቢና ወጪ ሸቀጦችን የሚያጓጉዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሥራቸው በምን ኹኔታ ላይ ይገኛል? የሚለውን ጨምሮ ፤ በነዳጅ እጥረት ቀውስ በሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖን የተመለከቱ ዘገባዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮቻችን ናቸው ።
    20 min
  • DW Amharic የመጋቢት 22 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    የኢራኑ ጦርነት የኢትዮ-ኤርትራን ውጥረት ያባብሰዋል ብለው እንደማያምኑ ተንታኞች ተናገሩ፤ እስካሁን የተቋረጠ የአገር ውስጥም ሆነ ዓለማቀፍ በረራ አለመኖሩንም ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡ የቅድስት ክፍሌ መታሰቢያ የመንገድ ደሕንነት ትምሕርት፤ የነዳጅ ዕጥረት እያስከተለው ያለው ጫና፤ የኢራን ጦርነት በአውሮፓ ሐገራት ያሳደረው ጫና
    23 min
  • የመጋቢት 21 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዜና መጽሔት አራት ርዕሰ ጉዳዮች ይተነተናሉ እነርሱም
    በኦሮሚያ ክልል የተኩስ ድምጽ እንዲቆም የቀረበው ጥሪ ፣ በደቡብ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት የወልቂጤ ቅርንጫፍ FM 89.2 ሠራተኞች የስራ ማቆም አድማ ፣ በትግራይ ክልል ሀገራዊ ኹነቶችን ለማከናወን ያለው ወቅታዊ ኹኔታ እንዲሁም የሁቲዎች ጥቃትና ማስጠንቀቂያ በአፍሪካ ቀንድ ስጋት እንዲጨምር ማድረጉ የሚሉት ናቸው። ማኅደረ ዜና ለዛሬ ትኩረቱን የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ በኢትዮጵያ ያስከተለውን ችግር ላይ አድርጓል።
    20 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…