ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ዜና መጽሔት
    -ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለው ጥቃት
    -ስለምርጫ ዝግጅት ከአዲስ አበባ እና ከደሴ የተሰባሰበ የሕዝብ አስተያየት
    -ፈረንሳይ በአፍሪካ አዲስ አጋሮችን እየፈለገች ነው
    -የአሜሪካ ፕሬዝደንት የቻይና ጉብኝት እና የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት እና አዲስ የኤች አይ ቪ መድኃኒት ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ መታቀዱን ያስቃኘናል።
    29 min
  • የግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ከ30 በላይ መንገደኞች በታጣቂዎች መገደላቸዉን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል።የህወሓት አባላት ናቸዉ የተባሉ ታጣቂዎች ከራያ አለማጣ ከተማ 50 የቤተ-ክሕነት ተማሪዎች ማገታቸዉ ከደሴ ሲዘገብ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ሕብረት አንዳድ አካባቢ በመራጮች ምዝገባ ሒደት ሕግ መጣሱን አስታዉቋል።ዜና መፅሔቱ የትግራይ ጋዜጠኞች ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ ለመሔድ መገደዳቸዉን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
    19 min
  • የግንቦት 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዓለም ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፣-በዋግ ኸምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች አቤቱታ፤ ዓለም አቀፉ የፍልሰኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኞች በአደገኛው መስመር መጓዛቸውን አላቆሙም ማለቱ፤ የኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት፤ አብላጫ ድምጽ ወይስ ተመጣጣኝ? ፤ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የስብሰባ ትኩረት እንዲሁም ከመሬት ለአራሹ ትግል እስከ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዘለቁትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አቶ ዘገየ አስፋውንም የሚያስታውስ ጥንቅር አካቷል።
    22 min
  • የአየር ንብረት ለውጥ እየፈጠረ ያለውን ችግር ስለመቋቋም የመከረው ዓለም አቀፍ ስብሰባ
    የአየር ንብረት ለውጥ በአለም አቀፍ ደረጃ እየፈጠረ ያለውን ችግር መቋቋም ወይም ተጋላጭነትን መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ የሚጠቁም አለም አቀፍ ኮንፈረንስ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ተካሂዳል። በኮንፍረንሱ የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን ለመፍታት የሚያግዙ በርካታ የምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
    4 min
  • የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መፅሄት ጥንቅራችን
    -ለሰባተኛው ዙር ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በገንዘብ ድልድል ላይ ያቀረቡት ቅሬታ
    -የኢኮኖሚ ዕድገት መመዘኛ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታም ከግምት ማስገባት አለበት መባሉን
    -የአየር ንብረትን መቋቋም የሚያስችል የግብርና ቴክኖሎጂን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ስብሰባ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱን
    -የኢራን የሰላም ዕቅድ በአሜሪካ ውድቅ መሆኑን የተመለከቱ ዘገባዎች ተካተዋል።
    20 min
  • ፓርቲዎች የምርጫ ማስፈጸሚያ ገንዘብ አለቃቀቅ ላይ መዘግየት መኖሩን ገለጡ
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ድርጅቶች በመደበኛ ጊዜ ከሚለቀው ገንዘብ በተጨማሪ፣ በምርጫ ወቅት ለሥራቸው ማስፈፀሚያ የሚያከፋፍለው በጀት መዝግየቱ እንዳሳሰባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።ፓርቲዎች ቅሬታውን ያቀረቡት የጋራ ምክር ቤት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፤ የቅድመ ምርጫ ሂደት ሥራዎች ላይ ከፓርቲዎች ጋር በመከረበት ወቅት ነው።
    4 min
  • የኢራን የሰላም ዕቅድ በአሜሪካ ውድቅ የመሆኑ አንድምታ
    ኢራን፤የአሜሪካ ማዕቀቦች እንዲነሱ መጠየቅን ጨምሮ ባለ14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ በፓኪስታን በኩል አቅርባለች። የኢራን የሰላም ዕቅድ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከማራዘም ይልቅ ጦርነቱን በዘላቂነት መቋጨት ላይ ያተኮረ ቢሆንም፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ዕቅድ ተቀባይነት የሌለው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
    5 min
  • የኢኮኖሚ ዕድገት መመዘኛ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታም ከግምት ማስገባት አለበት-የተመድ ባለሙያ
    የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ እድገት መመዘኛዎች የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታም ከግምት ማስገባት አለባቸው ሲሉ አንዲት አንጋፋ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያና የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የአማካሪዎች ቡድን አባል ተናግረዋል።የእድገት ምዘናው፣ ማህበራዊ የእድገት መለኪያዎችን መመልከት እንዳለበት አሳስበዋል።
    4 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…