ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ጥሪ
    ነዋሪዎች ከአሸናፊው ፓርቲ ምን ይጠብቃሉ ?
    ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች፤ 1655 ዜጎች ደግሞ በምህረት እንዲለቀቁ ተደረገ
    ለአሜሪካዉያን የኤቦላ ማገገምያ ማዕከል ኬንያ ዉስጥ መገንባቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ እንዲሁም
    የአውሮፓ ህብረትና ደቡብ ኮሪያ፤ የሰሜን ኮሪይና ቻይና ጉባኤዎች
    24 min
  • የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    በዜና መፅሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችና እያሳወቀ እና ቅሬታዎችንም እያጣራ መሆኑን መናገሩ፣ ሰቆጣ የተጠለሉ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቃዮች ለረሀብ መጋለጣቸውን መግለፃቸው ፣ -ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ መቀጠሉ ፣ የኤቦላ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅኝት ስራዎች እንዲጠናከሩ መጠየቁ ፣ ዛሬ በሜክሲኮ የሚጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው ።
    በባህል መድረክ ለህክምና ወደ በጀርመን በመጣበት አጋጣሚ እና የስዕል እግዚቢሽን ያቀረበውን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላን እንግዳዉ አድርጓል።
    26 min
  • የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዜና መፅሔት
    ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት፣ ጋምቤላ ክልል ዳግም ያገረሸው የፀጥታ ስጋት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ24 የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት ይፋ ማድረግ መጀመሩ፤ ለመጪው ዓመት ከ2,3 ትሪሊየን በላይ ብር የመንግሥት በጀት መታቀዱ እንዲሁም የዲጂታል ገቢ እና አዲሱ ፈተና የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    19 min
  • የዜና መጽሔት፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ ፈደ,ራዊ መንግሥትና በህወሓት መካከል የናረዉን ዉጥረት ለማርገብ የአፍሪቃ ሕብረትን ሚና የሚቃኝ ቀለ ምልልስን ያስቀድማል።የትግራይ ወጣቶች በብዛት ከክክልሉ መዉጣታቸዉንና ምክንያቱን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።የትራፊክ አደጋ መደጋገምና መፍትሔዉ ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የኤርትራና የግብፅ ወዳጅነት ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም የሚኖረዉን በጎ መጥፎ ዉጤት በሚቃኘዉ ዘገባ ያሳርጋል።
    20 min
  • የሰኞ ሰኔ አንድ ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን
    አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ስጋት
    በትግራይ የየደረሰዉ የድሮን ጥቃት እና አካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች
    በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ያልሰጡ በሰሜንና ደቡብ ወሎ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ነገ ሰኔ 2 ቀን የምርቻ ድምፅ ሊሰጡ መሆኑ ፤ እንዲሁም
    ኢሰመኮ - አርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ምዕመናን እና ቤተክርስትያን ላይ የተፈፀመ ጥቃትን በተመለከተ ክትትል እና ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለፁ በሚሉ ርዕሶች የተቀናበሩት በስፋት ይተነተናሉ።
    22 min
  • የግንቦት 27 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄት
    በዜና መጽሔት በአርሲ ዞን የተገደሉ ወገኖችን በሚመለከት የመንግሥት እና መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ምላሽ፤በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሔራዊ አስተዳደር የጻግብጂ ወረዳ በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ገብቷል መባሉ፤ግንቦት 24 ቀን ስለተካሄደው ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት፤ ድኅረ ምርጫ በደቡብ ሕዝቦች ክልል ፤ በሰባተኛው ምርጫ የተሳተፈው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ድሬደዋ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ችግር ደርሶብኛል ማለቱ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት IMF ለኢትዮጵያ 468 ሚሊየን ዶላር ለመልቀቅ መስማማቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።
    28 min
  • የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ከምርጫ ማግሥት ማን ምን አለ? የተሰጡ አስተያየቶች፤ በአርሲ የተፈጸመው ግድያ እና የቀረበው አቤቱታ፤ የአፍሪቃ ሕብረት፣ የኢጋድና የኅብረት-ለምርጫ የመጀሪያ ጊዜ ዘገባ፣ የአማራ ክልል ወጣቶች ጥሪ ከምርጫው ማግስት በኋላ፤ ብርን ያዳከመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሰኞው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። ድህረ ምርጫ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ቃለ መጠይቅ
    34 min
  • ልዩ ዝግጅት፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ማክሰኞ
    በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ዛሬ በየአካባቢው የወጡ ጊዜያዊ ውጤቶችን እንዲሁም የምርጫውን ሂደት፣ የፀጥታ ችግሮችና እና ተያያዥ ክስተቶችን የሚቃኙ ዘገባዎችን ያካተተ ልዩ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል። በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ትናንት የካቢኔ አባላት እና የዞን አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሹመቶችንም ማጽደቁን መነሻ ያደረገ ዘገባም አለን።
    47 min
  • በምርጫ ከሚያሸንፈው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?
    ትናንት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በመጭው አመስት አመታት የሚያስተዳድራቸውን ለመምረጥ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል። ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊው አካል በቀጣይ አምስት አመታት ሀገሪቱን የማስተዳደር ሀላፊነት ይጣልበታል።ለመሆኑ ከመጭው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?
    5 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…