የሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
ሱዳን የሚገኙ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ስደተኞች የከፋ አደጋ ላይ ናቸው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አሳሰበ። ከመካከላቸው ገዳሪፍ ያሉ ከ40 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ይገኙበታል ።
ከግንቦት አንስቶ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በደቡብ ሱዳን መንግስትና በተቃዋሚዎች ተወካዮች መካከል በኬንያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ሊጠናቀቅ ሲል ተሰናከለ።
የኔቶ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የአየር መከላከያ ስርዓት ለመለገስ ቃል ገቡ።