የዜና መፅሔት ጥንቅራችን የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን «አሥጊ» ያለችዉ ዉዝግብ የሚቃለልበትን ብልሐት የሚያፈላልግ የሽምግሌዎች ቡድን ጠቅላይ ሚንስትር ዓሕመድን እንዲያነጋግር ማቀዷን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል። የኢትዮጵያና የሩሲያ የመገበያያ ገንዘቦች ብርና ሩብል የቀጥታ ልዉዉጥ ወይም ምንዛሪ መጀመራቸዉን የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ጋምቤላ ክልል መግባታቸዉን የሚያዳስሰዉ ዘገባ ያስልሳል።