በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ትናንት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ መካከል ከፍተኛ ውጊያ እንደነበር ተሰማ።
እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለው ጽንፈኛ ቡድን አባላት መሆናቸው የተጠረጠ 82 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሔራዊ የስለላና የደኅንነት አገልግሎት ዐሳወቀ።
በአፋር ክልል አፍዴራ ከተማ ትናንት ምሽት የጣለዉ ብርቱ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ለአንድ ሰዉ ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነ፤ 31 ሰዎችም ተጎዱ። በሺህዎች የሚቆጠሩም ተፈናቅለዋል።
የኬንያ መንግሥት ለበርካታ የአፍሪቃ እና የካሬቢያን ሃገራት የይለፍ ፈቃድ መስፈርቶችን አነሳ።