ከትናንት በስተያ የተገደሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፖለቲከኛ በቴ ዑርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ በትውልድ ከተማቸው መቂ ተፈጸመ። በትግራዩ ጦርነት ወቅት ሞተዋል ተብለው ቤተሰቦቻቸው የተረዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ፣በቀይ መስቀል በኩል ከቤተሰቦቻቸው ጋር በስልክ መገናኘታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዶቼቬለ ተናግሩ። እነዚህና የኢትዮጵያ የውኃ መማክርት ጥሪ፣ የአውሮጳ ፓርላማ ያጸደቀው አዲስ የፍልሰት ሕግ እንዲሁም የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ በጆርጅያ የዓለም ዜናን የሚከተለው የዜና መጽሔት የሚዳስሳቸው ጉዳዮች ናቸው።