*ባለፈው ሰኞ በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል የቅድመ ካንሰር ምርመራ የተደረገላቸውና በእሥር ላይ ያሉት አቶ ክርስትያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬም ሆስፒታል ሳይወሰዱ መቅረታቸው ተነገረ ።
*በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድን «አዲስ» ያለውን የትግል አቅጣጫ እንደሚከተል ዐሳወቀ ።
*በውጭ አገራት የርዳታ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ከ280 በላይ ሠራተኞች ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ብቻ መገደላቸው ተገለጠ ።
*ጀርመን ውስጥ ከማኅበረሰቡ ጋር ያልተዋሐዱ ሶሪያውያን ሊባረሩ ይገባል ሲሉ አንድ ከፍተኛ ፖለቲከኛ ተናገሩ ።