የዓለም ዜና

የሕዳር 22 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መግደሉን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ወነጀለ። ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በወረዳው ሦስት መንደሮች በሁለት ቀናት በፈጸሟቸው ጥቃቶች በትንሹ 36 ሰዎች መገደላቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲያፈላልግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው ኮሚቴ የለያቸውን ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ይፋ አደረገ። በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀብ እንዲነሳ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ሲወስን ሶማሌላንድ ተቃወመች። የቅዳሜ የዓለም ዐበይት ዜናዎችን ያድምጡ!
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW