*«በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር» የተባለ ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ ።
*የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀመረ ። *260 ግድም ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ የየመን የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ የአደን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ሰጥማ ቢያንስ 49 ሰዎች መሞታቸው ተገለ ። ጀልባዋ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ስደተኞችን አሳፍራ ከሶማሊያ የባሕር ጠረፍ 320 ኪሎ ሜትሮች ቀዝፋ እንደነበር አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል ።