-አንድ ሰሞን ፍቅራቸዉ አለቅጥ ፀንቶ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአሥመራ ገዢዎች ጠብ ሰሞኑን የተካረረ መስሏል።የቃላት እንኪያ ሰላምቲያዉ አይሏል።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች ሥለ ወደብና የባሕር በር ማንሳታቸዉ ያሳሰባት ኤርትራ የኢትዮጵያን ጥያቄ «ሐሰት፣ ኋላ ቀር» እና ለኤርትራ «አስጊ» ብላዋለች።
-እስራኤል ከፍልስጤሙ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሐማስ ጋር ያደረገችዉን የተኩስ አቁም ሥምምነት ጥሳ ጋዛ ሰርጥን መደብደቧን ቀጥላለች።---የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት በስልክ ያደረጉት ዉይይትና የደረሱበት መግባባት ድጋፍም ጥርጣሬም አስከትሏል።