-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኮምፒዉቴር ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ደንበኞቹ አላግባብ ያዘዋወሩ ወይም ያወጡትን በቢሊዮን የሚቆጠር ብርለማስመለሥ እየጣረ መሆኑን አስታወቀ።ባንኩ ባለፈዉ አርብ ማታ ባጋጠመዉ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ደንበኞቹ የራሳቸዉ ያልሆነ 2.4 ቢሊዮን ብር አዘዋዉረዋል ወይም አዉጥተዋል።-ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ በታጣቂዎች ታግተዉ የነበሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለዉ አስከሬናቸዉ ተጥሎ መገኘቱን ቤተሰቦቻቸዉ አስታወቁ።የሟች ቤተሰቦች እንዳሉት ሠራተኞቹ ከታገቱ በኋላ አጋቾቹ ገንዘብ እንዲከፈላቸዉ ጠይቀዉ ከቤተሰቦች ጋር በመደራደር ላይ ነበሩ።