-ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ባካባቢዉ ሚሊሺያና ከሌላ አካባቢ የመጡ በተባሉ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ዉጊያ በትንሽ ግምት 10 ሰዎች ተገደሉ።ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተደረገዉ ዉጊያ ዛሬ ጋብ ማለቱ ተነግሯል።-የሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ለረሐብ ያጋለጠዉ ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ፣ ረሐቡም ወደ ጠኔ እየከፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የርዳታ ድርጅቶች ባለሥልጣናት አስታወቁ።ባለስልጣናቱ እንዳሉት አንዳድ አካባቢዎች ሕፃናት በረሐብና ረሐብ በሚያስከትለዉ በሽታ እየሞቱ ነዉ።-የአረብ እና የዩናይትድ ስቴትስ ሚንስትሮች የጋዛ ጦርነትን «ላጭር ጊዜ ለማስቆም» ያሉትን ስብሰባና ዉይይት እያደረጉ ነዉ።