-የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ኃይል በአማራ ክልል አድርሶታል ተብሎ የሚጠረጠረዉን የጦር ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲያጣራ ሁዩማን ራይትስ ወች ጠየቀ።የመብት ተሟጋቹ ድርጅት እንደሚለዉ የመንግስት ወታደሮች አማራ ክልል መራዓዊ ከተማ ዉስጥ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ገድለዋል።ሐብት ንብረት አዉድመዋልም።
-የኢትዮጵያና የሶማሊያ የዲፕሎማሲ ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ሶማሊያ ዛሬ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር አባርራለች።የራስዋን አምባሳደርም ከአዲስ አበባ ጠርታለች።ፑንትላንድና ሶማሊላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ቆስላ ፅሕፈት ቤቶች እንዲዘጉ አዝዛለችም።የፑንትላንድ ከፍተኛ ባለስልጣናት አዲስ አበባን እየጎበኙ ነዉ።