ትናንት ጠዋት በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በዳሞት መሰናዶ ትምህርት ቤት ውስጥ በተጣለ ቦምብ 31 ተማሪዎች መቁሰላቸው ተሰማ።
ከምሥራቅ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ደብረብርሀን በመጠለያ ስፍራ ቆይተው የተመለሱ ዜጎች ወደ ገጠር ቤታቸው ገብተው መሥራት እንዳልቻሉ አመለከቱ።
የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር የ1,7 ቢሊየን ዶላር ብድር መፈራረሙን የፋይናንስ ሚኒስቴር አስታወቀ። የፓሪስ ክለብ አበዳሪ ሃገራትም ለኢትዮጵያ የሰጡትን የጊዜ ገደብ እስከ ሰኔ መጨረሻ ማራዘማቸው ተነገረ።
እራስ ገዞቹ ፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥት የቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች እንዲዘጉ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ አስታወቁ።