የዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለመተባበር ቁርጠኛ ሆና እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር ተናገሩ። ኤርትራን ጨምሮ ከሌሎች ሁሉም አጎራባች ህዝቦች ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እንደሚሰሩ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ያለፈው ቅዳሜ በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ጥራታቸውን ሳይጠብቁ ወደ ውጪ የሚላኩ ቡናዎች ኢትዮጵያ ከዘርፉ ተገቢውን ገቢ እንዳታገኝ ማድረጉን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡