በሞቃዲሾ በሚገኘው ጎድካ ጂልኮው እስር ቤት ላይ ትላንት ቅዳሜ ጥቃት የፈጸሙ ሰባት የአል-ሸባብ አባላት መገደላቸውን የሶማሊያ መንግሥት አስታወቀ። እስራኤል እና ሐማስ የጋዛ ጦርነት በሚያበቃበት እና ታጋቾች በሚለቀቁበት መንገድ ላይ ነገ ሰኞ በግብጽ ሊደራደሩ ነው። ሩሲያ በሚሳይሎች እና ድሮኖች በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። በሺር አል አሳድ ከሥልጣን ከተባረሩ ወዲህ በሶርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገሪቱ ምክር ቤት ምርጫ ሲካሔድ ዋለ።