የዓለም ዜና

የመስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና


Listen Later

በደቡብ ምዕራብ ዳርፉር ውስጥ የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በአስቸኳይ ለውይይትም እንዲቀመጡ ጠይቃለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ አውሮፕላን የመን አቅራቢያ መከስከሱን ፔንታገን አረጋገጠ። የየመን ሁቲ ሚሊሺያዎች ባለፉት ቀናት በርካታ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን አስታውቀው ነበር።
ሊባኖስ ውስጥ በድምፅና መልእክት መቀበያ መሣሪያ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ እየተነገረ ነው።
ማዕከላዊ አውሮጳን ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ያጥለቀለቀው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከሮማንያ እስከ ፖላንድ ከባድ ውድመት አስከትሏል።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW