የዓለም ዜና

የሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና


Listen Later

የሰላም ሚኒስትር ደኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬ ዕለት የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።
ታንዛኒያ ውስጥ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ155 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ። እስያ ውስጥ ደግሞ በሙቀት ማዕበል ሰዎች እየሞቱ ነው። ቱርክና ግሪክ ከሰሃራ በመጣ አቧራ አየራቸው ታፍኗል።
በማዕከላዊ ናይጀሪያ ከባድ ዝናብ በእስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ 120 የሚሆኑ እስረኞች ማምለጣቸው ተሰማ።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም የወባ በሽታ ስርጭት በእጅጉ መስፋፋቱ እና የሚያደርሰው ጉዳትም እየከፋ መምጣቱ ተገለጸ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW