-በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የክልሉን የግንባታ ሥራና እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉን ባለሙያዎችና ሠራተኞች አስታወቁ።ባለሙያዎች እንዳሉት በግንባታ መስክ የተሰማሩ አብዛኞቹ ባለሐብቶች ወደ አዲስ አበባ ሸሽተዋል።-ባለፈዉ የካቲት ጀርመን ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ የመጀመሪያና ሶስተኛዉን ደረጃ የያዙት የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣማሪ መንግስት ለመመሥረት ተስማሙ።-----ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም የንግድ ተሻራኪዎችዋ ጋር የገጠመችዉ የንግድ ጦርነት እየተባባሰ ነዉ።አንዳድ መንግስታት ከፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር ለመደራደር ጠይቀዋል።ቻይና ግን በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ አፀፋ ቀረጥ ጥላለች።