-ኢትዮጵያ ዉስጥ መብታቸዉን ለማስከበር በሚጠይቁ ሠራተኞች ላይ አሠሪዎች የሚደርሱት ጫናና በደል እንዲቆም የሐገሪቱ የሠራተኛ ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጠየቀ።---የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፀጥታ አስከባሪዎች ለሱዳን መከላከያ ጦር ሊላክ ነበረ ያሉትን በሚሊዮን የሚቆጠር ጥይት መያዛቸዉ ተነገረ።የሱዳን መከላከያ ጦር ግን የአቡዳቢን መግለጫ በሱዳን ሕዝብ ዓይን ዉስጥ አዋራ ለመሞጀር የተቃጣ ዉሸት በማለት አጣጥሎ ነቅፎታል።---የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰዓዳ-የመን ዉስጥ ባደረሰዉ የአዉሮፕላን ጥቃት የአፍሪቃ ሥደተኞች የተጠለሉበትን ማቆያ ጣቢያ አወደመ።የየመን ባለሥልጣናት እንዳሉት በድብደባዉ 68 ሰዎች ተገድለዋል።