የዓለም ዜና

የነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና


Listen Later

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው በተባለ ጥቃት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።
ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ውስጥ ለሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤቷ አዲስ አምባሳደር ሾመች።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኢትዮጵያን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ3,600 በላይ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ መልቀቁን አስታወቀ። ከታሰሩ የኦነግ አባላት የተለቀቀ የለም።
የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ማረፋቸውን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW