በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጋብ ብሎ የነበረው ውጊያ ማገርሸቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። ለቀናት ተኩስ እንዳልነበረ የገለጹት እማኞች ዛሬ ከቀትር በኋላ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ የተለያየ አካባቢ ተኩስ መከፈቱን አመልክተዋል።
ቻይና በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለአፍሪቃ ሃገራት ከ50 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቷን አስታወቀች።
ከሱዳን ተፈናቅለው በኢትዮጵያ ተጠግተው ከነበሩ ስደተኞች 700 የሚሆኑት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነገረ።
በጀመርኗ ሙኒክ ከተማ በዛሬው ዕለት ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪን ተኩሶ መግደሉ ተነገረ።