ከአቶ እስክንድር ነጋ ፣የአማራ ህዝባዊ ግንባር መሪ ጋር የየተደረገውን ቃለ መጠይቅ ያስቀድማል ። በኦሮምያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን አራት ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኅይሎች ተግደለዋል ሲሉ ነዋሪዎች መናገራቸው፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአማራ ክልል ስለሚፈጸሙ የጅምላ እሥሮች እና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ዝምታን መምረጡን መውቀሱ እንዲሁም ዳግም መፈናቀል ያሰጋቸው የአዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈናቃዮች ዜና መጽሔት ዛሬ የሚያተኩርባቸው ርዕሶች ናቸው