DW Amharic ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ምርጫ የመሃል ቀኙ የአውሮጳ ህዝቦች ፓርቲ የተሻለ ወንበር በማግኘት ተጠናቀቀ። የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ፓርቲ ኢፒፒ ከ720 የፓርላማ መቀመጫዎች 189ኙን በማሸነፍ ፕሬዚዳንቷ በኃላፊነታቸው መቀጠል የሚያስችላቸውን መደላድል ፈጥሮላቸዋል ተብሏል። ምርጫው የአርንጓዴ እና ሊበራል ፓርቲዎች በርካታ መቀመጫዎችን ሲያጡ የቀኝ እና ግራ አክራሪዎች ግን ከምንጊዜውም ይልቅ ተጠናክረው የመጡበት እንደነበር የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል። «ምርጫውን አሸንፈናል» ሲሉ የተደመጡት የህብረቱ ፕሬዚዳን