በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች በሞተር ሳይክል ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።-በድሬደዋ የሚስተዋለው የሙቀት መጨመር ነዋሪውን ምቾት ሲነሳ እንደ ደም ግፊት ባሉ በሽታዎች ለሚታመሙ ሰዎች ስጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናገረዋል።/በኢትዮጵያ በተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ ስጋት እንዳላቸው በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተናገሩ፡፡-የአውሮጳ ህብረት 27 አባል አገሮች ከትናንት ሐሙስ ጀምሮ የፓርላማ ወኪሎቻቸውን እየመረጡ ነው።