-ኢትዮጵያ ዉስጥ «ሑከትና ብጥብጥ በመፍጠርና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትን በመናድ» ተጠርጥረዋል የተባሉ 9 እስረኞች ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀረቡ።ተጠርጣሪዎቹ አዋሽ አርባ ከሚገኘዉ እስር ቤት በቅርቡ አዲስ አበባ ወደሚገኘዉ ፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት የተዛወሩ ናቸዉ።-ለዘንድሮዉ ሐጂ ከ1.5 ሚሊዮን የሚበልጡ ምዕመናን ከሙስሊሞቹ ቅድስት ከተማ መካ ገቡ።-ጋዛን የሚያወድመዉን ዉጊያና ወታደራዊ ዘመቻ ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስና የአረብ ተከታዮችዋ የሚያደርጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዛሬም ለዉጤት አልበቃም።