የሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
ትናንት በአዲስ አበባ ከተማና በሌሎች ከተሞች ወደ ተሃድሶ ማዕካላት በሚያመሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተከፈተ የተኩስ እሩምታ ድንጋጤ መፍጠሩን የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። በተኩስ እርምታው ነዋሪው ላይ ለተፈጠረው ድንጋጤና ረብሻ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይቅርታ ጠይቋል።
ከሀገራቸው የሸሹት የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ሞስኮ ናቸው መባሉን ክሬምሊን ከማረጋገጥ ተቆጠበች።
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ በአማጽያኑ ከተገለበጡ በኋላ ጀርመን የሶሪያ ዜጎች የተገን ጥያቄዎች ላይ የሚሰጡ ውሳኔዎችን ለጊዜው እንደምታቆም አስታወቀች።