በሱዳን በምትገን የዲሊንጅ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 7 ስቪሎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ። የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ «በኢራን ይደገፋል» ያለው የሒዝቦላህ አባላት ናቸው ያላቸውን 3 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ። በአውስትራልያ ቦንዲ በተበለ የባሕር ዳርቻ 2 ጠመንጃ የታጠቁ ግለሰቦች ዘመናት ያስቆጠረውን ባሕላዊ ክብረበ ዓላቸውን ሲያከብሩ በነበሩ ይሁዲዎች ላይ ዛሬ በፈጸሙት የተኩስ እሩምታ ቢያንስ 12 ሰዎች መሞታቸውን ተሰማ።