የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ አረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ (ባይቶና) ኪዳን ለሥር ነቀል ለውጥ የተባለ ጥምረት መሰረቱ። በአማራ ክልል በዋግሕምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በተከሰተ ድርቅ ከ85 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የየአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ገለጹ። በሐድያ ዞን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላልተቀጠሩ ሠራተኞች ደሞዝ ይከፍላሉ ሲሉ ነዋሪዎች ወነጀሉ።