የዓለም ዜና

የታኅሳስ 29 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ ሞሐመድ ከኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለመነጋገር አስመራ ገቡ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ዛሬ ሰኞ ከሶማሌላንድ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ኑር ኢስማኤል ታኒ ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተዋል። በላይቤሪያ የነዳጅ ማጓጓዣ ቦቴ ሲፈነዳ የገደላቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 74 ማሻቀቡን የሀገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። በኢራን የሚደገፈው የሒዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ በደቡባዊ ሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ። የጀርመን መንግሥት በሒደት የግብርና ድጎማ ለማቋረጥ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ የወጡ ገበሬዎች በትራክተሮቻቸው መንገድ ዘጉ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW