የታኅሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ መንግሥት የመብቶች እና ዴሞክራሲ ማዕከል የተባለውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ዳግም «ከማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ» አገደ።
የአውሮጳ ኅብረት በሶሪያ ላይ የጣላቸውን አንዳንድ የኤኮኖሚ ማዕቀቦች ማንሳትን እንደገና ሊያጤን እንደሚችል አስታወቀ።
የፈረንሳይ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ በሙስና እና ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ተከሰው የተበየነባቸውን ውሳኔ አፀና። ፍርድ ቤቱ ሳርኮዚ እንቅስቃሴያቸውን የሚከታተል የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ለአንድ ዓመት እንዲያደርጉም አዟል።