የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ጦር በድንበር አካባቢ ባሉ ሁለት ከተሞች ላይ ጥቃት አድርሶብኛል ሲል ከሰሰ። ክሱን አስደንጋጭ ያለው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ሀሰት ነው ሲል አስተባብሏል። ድርጊቱ የሁለቱን ሃገራት ጤናማ ግንኙነት ለማበላሸት ባለሙ ኃይሎች የተፈጸመ ነውም ብሏል።
ቀጠር ሶርያ ላይ የተጣለው ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ባስቸኳይ እንዲነሳ ጠየቀች።
16 ሰዎች አሳፍራ የነበረች አንድ የሩሲያ ዕቃ ጫኝ መርከብ ስፔን አቅራቢያ መስመጧ ተሰማ። ከተሳፋሪዎቹ ሁለቱ አልተገኙም።
የአሜሪካ አየር መንገድ ጠቅላላ በረራዎቹን የቴክኒክ ችግር ባለው ምክንያት ማቋረጡን ዛሬ አስታወቀ።