ከ48 ኢንቨስተሮች 1.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የድርሻ ድልድል እያካሔደ ነው። በዚህ ሣምንት የሚጠናቀቀው ድልድል ባለድርሻዎች ምን ዓይነት መብት እንደሚኖራቸው ይወስናል። የናይጄሪያ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የቦርድ አባል እንደሚሆኑ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ሲጀምር ግብይቱ የሚመራበትን ሕገ-ደንብ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ግብይት የሚካሔድበትን ቴክኖሎጂ ለመዘርጋት አቅራቢዎች የሚመርጥበት ደረጃ ላይ ነው።