በዛሬው የዓለም ዜና፤በደቡብ ሱዳን ዳግም የተከሰተው ግጭት ከ180,000 በላይ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉን፣በዩናይትድ ስቴትስ ከ 600,000 በላይ ደንበኞች በክረምት አውሎ ንፋስ ምክንያት የኤለክትሪክ ኃይል ማጣታቸውን እና ከ10,000 በላይ የሚሆኑ ለዛሬ እሁድ የታቀዱ በረራዎችም መሰረዛቸውን፣ኢራን በተፈጠረው አለመረጋጋት በሁለት ቀናት ውስጥ 30,000 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል መባሉን፣በኢራን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት፣ ተመራጭ አይደለም ስትል ፈረንሳይ ማስታወቋን እንዲሁም በዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጥሪ ማቅረባቸውን ይስቃኛል።