ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ እርዳታን ማቆማቸው አፍሪቃ ውስጥ ድንጋጤ አስከትሏል። USAID በአሜሪካም ሆነ በውጪው ለሚገኙ ሠራተኞቹ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ አስተዳደራዊ እረፍት መስጠቱን ይፋ አድርጓል።
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ክልሉን ከትግራይ የሚያገናኘው የብረት ድልድይ ትናንት በደረሰበት ጉዳት አገልግሎት መስጠት ማቋረጡ ተገለጸ።
ፍልስጤማውያን ከአካባቢው ሳይለቁ ባስቸኳይ ጋዛ መልሶ እንዲገነባ ግብፅ ጥሪ አቀረበች። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋዛን የማስተዳደር ዕቅድ ከወዲሁ ጠንካራ ትችት ገጥሞታል።
የዩጋንዳ ፖሊስ የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ መረጃ መጠለፉን ተከትሎ ዘጠኝ የፋይናንስ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አሠረ።