የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ትናንት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ መደረጉን ቤተ ክርስትያኗ አአረጋገጠች። በኦሮሚያ ክልል ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የገበያ እና የመጓጓዣ አድማ ከጠራ 10 ቀናት በኋላ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በዚህ ወር መጨረሻ ሊካሔድ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለት የነበረውን ምርጫ በማራዘማቸው በሀገሪቱ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።