አርስተ ዜና፤
-በዴሞክራቲክ ኮንጎ ጦር እና በሩዋንዳ ይደገፋል በሚባለው የM 23 አማጺዎች መካከል ውጊያው መባባሱ ተነገረ። ኮንጎ በሲቪሎች ላይ ለደረሰው ግድያ እና አስከፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የተመድ ሩዋንዳን ተጠያቂ ያድርግልኝ ብላለች። --በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መኪና በማስቆም በተደረገ እገታ አንድ ሰው ተገደለ፤ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን የዓይን እማኝ ተናገሩ።--የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ላይ የጣሉትን እገዳ በርካታ ሃገራት ተቃወሙ። ትራምፕ የICCን ንብረት በማገድ፤ ባለሥልጣናቱ፣ ሠራተኞቹ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የጉዞ እገዳ ጥለዋል።