የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ በመጪው ሐሙስ በዩጋንዳ በሚካሔደው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን አስታወቁ። አሜሪካ በየመን የሑቲ አማጽያን ዒላማዎች ላይ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት የአየር ድብደባ ፈጸመች። ጋና ከኦፊሴያል አበዳሪዎቿ ጋር የ5.4 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ ሥምምነት ላይ ደረሰች። እስራኤል በጋዛ ለሊቱን በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 60 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ። በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት የሚካሔደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል።