የኦሮሚያ ክልል ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አራት ዐቃቢያነ ሕግ ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው አንዱ መገደላቸውን የክልሉ ዐቃቢያነ ሕግ ማኅበር አስታወቀ።
ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ በምርጫ ቦርድ የተሰረዘበት ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት ጠየቀ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪ አካላት ስምምነቱን ከዳር እንዲያደርሱም ጥሪ አቀረበ።
የአፍሪቃ ሕብረት በዛሬው ዕለት የጊኒ ቢሳው ፕሬዝደንት ባስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ጠየቀ።
ሆንግ ኮንግ ውስጥ በደረሰው የእሳት አደጋ የሞቱት ቁጥር 65 ደረሰ። በአደጋው የተጎዱት 71 ደርሰዋል። ከ200 በላይ ደግሞ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።